በአደይ አበባ መኖሪያ ግቢ የነዋሪዎች ትውውቅ ለመልካም ጉርብትና

የዚህ ግቢ ነዋሪዎች አሁን በተቀበልነው አዲስ ዓመት ህብረታቸውን በይበልጥ በማጠናከር እሁድ መስከረም 9 2014 አንድ ላይ ሆነው ደማቅ የመተዋወቂያ ዝግጅት አድርገዋል፡፡ ይህ ዝግጅት ትልቅ ትንሽ ሳይል ሁሉንም በሚያሳትፍ እና በሚያነሳሳ መልኩ በቅርብ ጊዜ በተቋቋመው የነዋሪዎች ኮሚቴ አስተባባሪነት የተዘጋጀ ሲሆን ነባር እና አዲስ ነዋሪዎችን አሳትፏል፡፡ የዝግጅቱ አላማ በዋነኝነት ነባር ነዋሪዎችን ከአዲስ ነዋሪዎች እንዲሁም የኮሚቴ አባላት ጋር በይበልጥ ለማስተዋወቅ እና ወደፊት በአንድነት መስራት እና መድረስ ስላለባቸው ክንውኖች እንዲወያዩ ነው፡፡ በግቢው ያሉ ነዋሪዎች ከተለያየ ቦታ እና ቤተሰብ የመጡ ቢሆኑም በአደይ አበባ ግቢ ግን ልዩነታቸውን ትተው ለልጆቻቸው ተምሳሌት ለመሆን መልካም ምግባርን የሚያንፀባርቅ ታላቅ ማህበረሰብ እንዲመሰርቱ የኮሚቴው አባላት መልዕክታቸውን አስተላፈዋል፡፡ በዝግጅቱ አዋቂዎች በአንድ በኩል የሚጨዋወቱበትን አካባቢ በመፍጠር በአንድ በኩል እንዲሁም ለልጆች እንደ እድሜያቸው የተለያዩ መጫዎችን በማሟላት መልካም ጊዜ እንዲያሳልፉ ኮሚቴው አመቻችቷል፡፡ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት በምሳ ፕሮግራም የጀመረው ይህ ዝግጅት ከነዋሪዎች በመልካም ፈቃደኝነት የተሰበሰቡትን አልባሳት ለተደራጁ የእርዳታ ተቋሞች ገቢ እንዲሆን ከነዋሪዎች በመሰብሰብ እና በታላላቆች ምርቃት እንዲሁም በነዋሪዎች መልካም ምኞት ምሽቱ ተጠናቋል፡፡
ዝግጅቱ እውን እንዲሆን ለቀናት ሲደክሙ እና ሲያስተባብሩ ለነበሩ ኮሚቴዎች፣ ለአካባቢው ወረዳ፣ ለለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ የፖሊስ መምሪያ፣ ለአጋር እና እህት ኩባንያዎች፣ ለነዋሪዎች፣ እንዲሁም በግል ተነሳሽነት የግቢውን አረንጓዴ ቦታ በማስዋብ ላይ ላሉ ግለሰብ ወ/ሮ ኒሻን የስኬታችን ተካፋዮች በመሆናቸው ልባዊ ምስጋናችንን ልናቀርብ እንወዳለን፡፡