በአደይ አበባ ሪል እስቴት ኃ/ የተ/ የግ/ ማህበር የነዋሪዎች መተዳደሪያ ማኅበር ተመሰረተ::

በአደይ አበባ ሪል እስቴት ኃ/ የተ/ የግ/ ማህበር ላለፉት 5 አመታት ከሀገር ውጭ እንዲሁም በሀገር ውስጥ ያሉ ቤት ፈላጊ ማህበረሰባችንን ስናገለግል ቆይተናል፡፡ መሪ ሎቄ በመባል በሚታወቀው ወረዳ ሰፍሮ 160 ቤቶችን የያዘ የአደይ አበባ ቁጥር አንድ ፕሮጀክትን በተሳካ ሁኔታ አስረክበን አሁን በያዝነው አመት ደግሞ 504 ቤቶችን በማጠናቀቅ ለደንበኞቻችን በማስረከብ ላይ እንገኛለን፡፡
ህንፃዎቻችንን ስንነድፍ ለነዋሪዎች የሚሆኑ አካባቢዎችን የኢኮኖሚ፣ የመሰረተ ልማት፣ ደህንነት፣ ማህበራዊ መዳረሻዎች የመሳሰሉትን ዘርፎች በጥልቅ በማጥናት በፍፁም ጥራት እና ብቁ ባለሞያዎች እጅ ዘላቂ የሆኑ ቤቶችን ገንብተን ለነዋሪዎቻችን በቃላችን መሰረት እናስረክባለን፡፡ ታድያ እምነታቸውን በእኛ ላይ ጥለው የተቀላቀሉንን በርካታ የአደይ አበባ ቤተሰቦችን ቆም ብለን ስናይ ፍፁም ኩራት ይሰማናል፡፡ በአደይ አበባ ሀላፊነታችን ገንበቶ በማስረከብ ብቻ አይወሰንም፡፡ ድርጅታችን አንድ አልሚ ከሚጠበቅበት በላይ በመሄድ ለነዋሪዎቻችን የንብረት አስተዳደርን በማመቻቸት፣ የካርታ ኮፒ ለእያንዳዱ ገዢ በማዘጋጀት፣ የውሀ ጉድጓድ በማስቆፈር ፓምፕ አስገጥሞ ለእያንዳንዱ ቤት ተደራሽ እንዲሆን በማድረግ እና ቆጣሪ በየቤቱ መዘርጋት የመሳሰሉትን ከስምምነት ውጪ የሆኑትን አገልግሎቶች በድርጅታችን ተነሳሽነት አከናውነናል፡፡
በ ግንቦት 15 2013 አዲሱ የአደይ አበባ መኖሪያ ግቢ ውስጥ የነዋሪዎች ማህበር መተዳደሪያ እና መመስረቻን አስመልክቶ አልሚው፣ የቤት ገዢዎች እንዲሁም ህጋዊ ተወካዮች በተገኙበት የመተዳደሪያ ረቂቁ ላይ ሰፋ ያለ የውይይት እና ውሳኔ ፕሮግራም ተካሂዷል፡፡ ውይይቱንም ተከትሎ ነዋሪዎች ከመካከላቸው አስመራጭ ኮሚቴዎችን በማዋቀር ከነባር ኮሚቴዎች ጋር በጋራ የሚሰሩ ተጭማሪ ግለሰቦችን ያካተተ ተላላፊ ኮሚቴ መስርተዋል፡፡ የዚህም ማህበር ዋና አላማ እንደሚከተለው ተቀምጧል፡
1. የማህበሩ አባላት የሆኑ የህንፃው ነዋሪዎችን ሰላም፣ ደህንነት፣ መብት እና ጤናን ማስጠበቅ፡፡
2. አባላት በየግላቸው በመኖሪያ ህንፃ ውስጥ እንዲደረግ ወይም እንዲሆን የሚፈልጉትን ነገር በማኅበሩ አማካይነት ማስፈጸም፡፡
3. ህግ፣ ደንብ፣ ሥርዓት እና ጨዋ የሆነ አኗኗር የሚሰፍንበት መንገድ በጋራ መቀየስ በማኅበሩ አማካይነት ተግባራዊ ማድረግ፡፡
4. በአፓርታማው ውስጥ የሚኖሩ አባላት ጤናማ እና መልካም ግንኙነት እንዲኖራቸው ማድረግ፡፡
5. በማኅበራቸው አማካይነት በህንፃው የዕለት ከዕለት የአስተዳደር ጉዳዮች ላይ መሳተፍ፡፡
6. ነዋሪዎች ከአካባቢያቸው የመስተዳደር አካላት ከመንግስት መሥሪያ ቤቶች እንዲሁም ከህንፃው ባለቤቶች መልካም አኗኗርን በሚመለከት የሚያነሷቸውን ገምቢ ጥያቄዎች እና እንዲሻሻል የሚፈልጉትን ነገር በማኅበሩ በኩል መጠየቅ፡፡
7. የተሻለ ጤናማ እና ሰላማዊ አኗኗር ለመኖር የሚያስችሉ እና የተሻሉ ቴክኖሎጂዎች ሲመጡ እነዚሁ በህንፃው ላይ እንዲተገበሩ የገንዘብ አስተዋፃኦ ማድረግ እና ገንዘቡ በስራ ላይ መዋሉን መቆጣጠር፡፡
8. አደይ አበባ ሪል እስቴት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር እና የነዋሪዎች ተወካዮች የአዘጋጁት ይህ ደንብ እና ከዚህ ደንብ ጋር ተያይዞ የደንቡ አካል የሆነው የውስጥ ደንብ በትክክል ሥራ ላይ የሚውልበትን መንገድ መከታተል እና ደንቡ እንዲሻሻል ሀሳብ ማቅረብ፡፡
9. የህንፃው ነዋሪዎች ሀዘን፣ አደጋ እና ችግር ሲደርስባቸው ነዋሪዎችን የማስተባበር እና በተመሳሳይ አኳኋን የተሻለ ማህበራዊ ግንኙነት እንዲኖር የመገናኛ የመተዋወቂያ የሽርሽር እና የጉዞ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት፡፡
10. ከፍ ሲል ከተጠቀሱት ዓላማዎች ጋር በቀጥታ ግንኙነት ያላቸውን ሌሎች ማኅበራዊ ፋይዳዎችን ማከናወን ናቸው፡፡

ABOUT US

Download our app

FIND US

Join us:

CONTACT US


security image
    Copyright © 2020. All rights reserved.